ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አብደዋልን?

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አብደዋልን?

By Nasrudin Ousman

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ኢስላማዊ መንግሥት የመመሥረት ዓላማ አንግቦ የሚንቀሳቀስ ቡድን አለ››የሚለው አባባል ለእኔ ትርጉም አልባ ነው፡፡ እውነት ነው ብዬ ለመቀበልም በጣም ይቸግረኛል፡፡ ይህን ከመሰለ የፈጠራ ወሬ የሚገኘው ፖለቲካዊ ትርፍ ምን እንደሆነም ፈጽሞ አልገባህ ብሎኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት የሚንቀሳቀስ ቡድን ካለ፣ ያንን ቡድን ከማንም በላይ እና በፊት አምርሮ የሚቃወም እና የሚያወግዘው ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ነው፡፡

ዶ/ር ጀይላን ለአል ጀዚራ ቴሌቪዥን በአረብኛ ሲናገሩ፣ ‹‹የበርካታ ሃይማኖት ተከታዮች በሚገኙባት ኢትዮጵያን የመሰለች አገር ኢስላማዊ መንግሥትን ስለመመሥረት ማሰብ እብደት ነው››ብለዋል፡፡ እኔን ጨምሮ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ይህን አባባል በእጅጉ እንጋራለን፡፡…በ1960ዎቹ አጋማሽ ‹‹የሃይማኖት እኩልነት ይከበር!››እያሉ በታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ የጮሁት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፣ በዘመነ ኢሕአዴግ፣ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ‹‹መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፤ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሃይማኖትም በመንግሥት ሥራ ላይ ጣልቃ አይገባም››ተብሎ በይፋ ሲደነገግ ከማንም በላይ ጮቤ የረገጡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፣ ዛሬ በዚህችው ኢትዮጵያ ኢስላማዊ መንግሥት የመመሥረት ዓላማ አንግበው ሊንቀሳቀሱ አይከጅሉም በእርግጥም ካላበዱ በስተቀር፡፡ አላበድንም! እደግመዋለሁኝ አላበድንም!!

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአገራችን ኢትዮጵያ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ክፉኛ ያስቆጣ፣ ክፉኛም ግራ ያጋባ አንድ ትልቅ ችግር ተፈጥሯል፡፡ በአሁኑ ሰአት ከችግሩ ጋር በቀጥታ እየተጋፈጥን ያለነው እኛው ሙስሊሞቹ ብቻ ብንሆንም ቅሉ፣ ችግሩ ግን ቆም ብሎ በሰከነ አዕምሮ የሚያስብ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚመለከት፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ብቻ ሳይሆን እርሱንም ሊያስቆጣ የሚችል ወይም የሚገባው ነው ብለን እናምናለን፡፡ …ሙስሊም ያልሆነው ኢትዮጵያዊ ወገናችን የችግሩን ጥልቀት እና ክብደት ይረዳ ዘንድ ራሱን አንድ ጥያቄ ብቻ እንዲጠይቅ እንፈልጋለን ‹‹እንዲህ ዓይነት ነገር በእኔ ላይ ቢፈፀም ኖሮ አሜን ብዬ እቀበላለሁኝን?››…


እኮ እንዴት ያለ ነገር?

ችግሩ በሙስሊሞች የተፈጠረም አይደለም፡፡ በሙስሊሞች መካከል የተፈጠረም አይደለም፡፡ እውነቱን በገደምዳሜ ሳይሆን በግልጽ ለመናገር ችግሩ የተፈጠረው በመንግሥት እና በመንግሥት አማካይነት ብቻ ነው፡፡ በጥቅሉ ሲነገር፣ የችግሩ መሠረታዊ መነሾ የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ለማመን በሚያዳግት ድፍረት (incredible boldness) በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ‹ጭው ብሎ መግባት›ነው፡፡ ‹ጭው ብሎ መግባት›የሚለውን አገላለጽ የተጠቀምሁት፣ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱ አዲስ ስላልሆነ ነው፡፡ በሌሎች ሃይማኖቶች አኳያ ለመናገር ለጊዜው በቂ መረጃ ባይኖረኝም፣ ሙስሊሙን በተመለከተ ግን ቢያንስ ከ1987 ወዲህ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከኢሕአዴግ ቁጥጥር ውጪ ሆኖ አያውቅም፡፡ የጣልቃ አገባቡን ደረጃና መልክ ስናይ ግን የአሁኑ (በጥቅሉ ከ2000፣ በይፋ ደግሞ ከሐምሌ 2003 ወዲህ ያለው) እና የከዚህ ቀደሙ (ከ1987 –2000) የሰማይና የምድር ያህል የተራራቁ ናቸው፡፡ ጣልቃ አገባቡ እንዳሁኑ ፍፁም ጀብደኝነት የተመላበት ሆኖ አያውቅም፡፡

እንዳልሁት ላለፉት 17 ዓመታት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብም አንድያ የሃይማኖት ተቋሙ ከፖለቲካ መሣርያነት ባለፈ የማኅበረሰቡን መንፈሳዊ ህይወት ለማበልፀግ የረባ ሥራ አለመሥራቱ ሲያሳዝነው ቆይቷል፡፡ እንዲያም ሆኖ ቢያንስ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶቹን በመጠቀም እምነቱን በነፃነት ለማራመድ፣ ለመተግበር እና ለማስተማር የሚያደርገው የግል እና የወል ጥረት ስላልተስተጓጎለበት ከተቋሙ ብዙም ሳይጠብቅ በሰላም ኑሯል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የኢሕአዴግ መንግሥት አንዳችም የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ይሁንታ እና እውቅና ሳይጠይቅ፣ በዚሁ እርሱ በሚቆጣጠረው ‹‹የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተቋም››ላይ የ‹‹አሕባሽ››አስተምህሮ አራማጆችን በመሾም፣ ይህንኑ አስተምህሮ በ‹አሕባሻዊው›ጠቅላይ ም/ቤት አስፈፃሚነት፣ በኢትዮጵያ ሙስሊም ኅብረተሰብ ውስጥ ለማስረፅ (ለመጫን ወይም ለማስጫን) በትጋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በሚሊዮኖች የምንቆጠረውን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአሕባሽ አስተምህሮ የማጥመቅ ‹‹ተልዕኮ እና ሥልጣን››የተሰጠው ‹‹አሕባሻዊው ጠቅላይ ም/ቤት››ተልዕኮውን የሚፈጽመው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚያደርግለት ቀጥተኛ ድጋፍ እና የቅርብ ክትትል ነው፡፡

መንግሥት በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ተቋም ላይ የ‹አሕባሽ›አስተምህሮ አራማጆችን የሾመው በ2000 ቢሆንም፣ ም/ቤቱ በአሕባሽ አስተምህሮ የማጥመቅ ዘመቻውን በይፋ የጀመረው በሐምሌ ወር 2003 ሐሮማያ ላይ ባካሄደው የመጀመርያ የሥልጠና ጉባዔ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ኅብረተሰብ ‹‹እንዴ! ምን እየተሠራ ነው?!››ብሎ ማጉረምረም የጀመረውም ያኔ ነው፡፡ [በነገራችን ላይ ያንን ‹‹ታሪካዊ››የሥልጠና ጉባዔ በንግግር የከፈቱት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ነበሩ፡፡ ሥልጠናው በክቡር ሚኒስትሩ ንግግር መከፈቱ ግን ከየክልሉ ተጠርተው ሥልጠናውን ከታደሙ ወደ 1500 የሚጠጉ ሙስሊሞች፣ ከ500 የማያንሱት አቋርጠው ከመውጣት አላገዳቸውም፡፡ በነገራችን ላይ፣ ከሐሮማያው ሥልጠና በኋላም፣ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄዱ የ‹አሕባሽ›አጥምቆት ጉባዔዎች ላይ ሚኒስትሩ ‹‹ውድ ጊዜያቸውን ሰውተው››የመክፈቻ ንግግር ከማድረጋቸውም በላይ ሥልጠናው ሲጠናቀቅም ለሠልጣኞች የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡]

እርግጥ መንግሥት ‹‹በእነዚህ ሥልጠናዎች ላይ የምገኘው ለተሳታፊዎቹ በሕገ መንግሥቱ ዙርያ ግንዛቤ አስጨብጥ ዘንድ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስለተጠየቅሁ ነው››ሲል ነግሮናል፡፡ ለሐሮማያው ሥልጠና ከየክልሉ ከተጠሩት ሙስሊሞች መካከል 500 ያህሉ ‹‹ሥልጠናውን››አቋርጠው የወጡት፣ ‹‹ለምን ስለ ሕገ መንግሥት ግንዛቤ አስጨበጣችሁን?››ብለው ነውን? አይደለም፡፡ ውሎ ሳያድር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዳር እስከ ዳር ማጉረምረም የጀመሩትስ ‹‹ለምን ሕገ መንግሥቱ በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ እንዲሠርጽ ይደረጋል?››ብለው ነውን? አይደለም! መላው የአገሪቱ ሕዝብ ስለ ኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ቢጨብጥ፣ ሙስሊሞች ይደሰቱ እንደሁ እንጂ የሚያጉረመርሙበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ከሕዝቡ ግንዛቤ መጨበጥ የበለጠ ግን ሙስሊሞችን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያውያን ከልብ የሚደሰቱት መንግሥት ሕገ መንግሥቱን አክብሮ ቢያስከብር ነበር፡፡ ካለፉት በርካታ ወራት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያለማቋረጥ እያጉረመረሙ ያሉትም ይህ ባለመሆኑ ነው መንግሥት ሕገ መንግሥቱን በመጣሱ!

መንግሥት ከ1950ዎቹ ወዲህ በሊባኖስ ምድር በተቋቋመ ‹‹አሶሴሽን ኦፍ ኢስላሚክ ቻሪቲስ››(AICP) የሚባል የበጎ አድራጎት ድርጅት አማካይነት እየተሰበከ የሚገኘውን የ‹‹አሕባሽ››አስተምህሮ ‹‹ነባሩ እስልምና››ብሎ በማንቆለጳጰስ፣ ‹አሕባሻዊው›ጠቅላይ ም/ቤት ሙስሊሙን ኅብረተሰብ በአሕባሽ አስተምህሮ ለማጥመቅ ለሚያካሂደው ዘመቻ በቀጥታም በሉት በተዘዋዋሪ ይሁንታውን ችሯል፡፡ በአንጻሩ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ኅብረተሰብ ‹‹ሱፊዩም››ሆነ ‹‹ሰለፊዩ››ተቋማችን የ‹‹አህባሽ››አስተምህሮ ማስፋፊያ ሊደረግ አይገባም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የ‹‹አሕባሽ››ን አስተምህሮ የመቀበል፣ የመተግበር እና የማስተማር ሕገ መንግሥታዊ መብት አለው፡፡ ነገር ግን የእኛ ተቋም ለ‹‹አሕባሽ››አስተምህሮ አራማጆች ተላልፎ ሊሰጥ አይገባም፡፡ ፈጽሞ ያልመረጥናቸው የ‹‹አሕባሽ››አስተምህሮ አራማጆች ተቋማችንን ሊቆጣጠሩ፣ እምነታቸውንም በሰፊው ሙስሊም ሕዝብ ላይ ሊጭኑ አይችሉም፡፡ የመጅሊሳችንን መሪዎች የመምረጥ መብታችን ይከበር! እያሉ ‹‹ለመንግሥት ባልተመቸ››እጅግ ሰላማዊ መንገድ እየጮሁ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ለ‹‹ወዮልህ!››ዛቻ እና ማስፈራሪያ በርግጎ፣ ‹‹አክራሪ››እና ‹‹አሸባሪ››በሚሉ ቅጥያዎች ተሸማቆ ይህን ከመሠረታዊ የእምነቱ ጉዳይ ጋር የሚገናኝ ጥያቄ እርግፍ አድርጎ ይተዋል ተብሎ ይታሰባልን? ይህንን ጉዳይ አለቅጥ ለጥጦ በኢትዮጵያ ምድር ኢስላማዊ መንግሥት ከመመሥረት ጋር ማያያዝስ ምን ይጠቅማል? የትስ ያደርሳል? ይህንን የሙስሊሙ ሕዝብ ጥያቄ ተገቢነት ለመረዳት የግድ ሙስሊም መሆን አያስፈልግም፡፡ ‹‹እንዲህ ዓይነት ነገር በእኔ ላይ ቢፈፀም ኖሮ አሜን ብዬ እቀበላለሁኝን?››ብሎ ራስን መጠየቅ በቂ ነው፡፡

እስካሁን ከታየው ሁኔታ በመነሳት መንግሥት የሙስሊሙን ሕዝብ ጥያቄዎች ለማስተናገድ የመረጠው አካሄድ ለችግሩ እልባት የሚያስገኝ አይመስለኝም፡፡

በፕሮፓጋንዳው መስክ እየተሠራ ያለው ነገር ደግሞ እጅግ አሳፋሪ እና ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በባህር ማዶ የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአንድ ድምጽ እየጮሁበት ያሉትን ግልጽ የሕዝብ ጥያቄ ‹‹የጥቂት ስውር ዓላማ ያላቸው ግለሰቦች››አድርጎ ለማጣጣል መሞከር ነገሮችን ያካርር እንደሁ እንጂ ከቶውንም አያለዝብም፡፡ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው የህትመትና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ላይ የሚሠሩ ጋዜጠኞች፣ ‹‹በዚህ እና በዚያ አቅጣጫ ፃፉ››ስለተባሉ ብቻ፣ ጠለቅ ብለው በማያውቁት፣ ሥራዬ ብለውም ባልተከታተሉት ጉዳይ ላይ ጨርተው ጨርተው እላቂያቸው የቀረ ውል የለሽ ቃላትን በመደረት ኃላፊነት በጎደለው ተግባር ላይ ባይተጉ መልካም ነው፡፡ መንግሥት የያዘው አቋም አደገኛ ይመስለኛል፡፡ ይህንን አደገኛ አቋም በማራገብ እና በመለጠጥ ነገሮችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ መምራት ለአገራችን ሰላም አያመጣም፤ ልማትን አያፋጥንም፤ ዴሞክራሲን አያጎለብትም፡፡ የሕዝብን ድምጽ መስማት፣ ለሕዝብ ጥያቄም ተገቢውን ምላሽ መስጠት ነው የሚጠቅመው፡፡ ሕዝብን መናቅ ማንንም የትም አያደርስም፡፡

መነሻዬ ላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ካላበዱ በቀር በኢትዮጵያ ኢስላማዊ መንግሥት ስለመመሥረት ሊያስቡ አይችሉም ማለቴን ታወሰኝ፡፡ አሁን ጽሑፌን ልዘጋ ስል ደሞ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የማያደርጓቸው ሌሎች ሁለት ነጥቦች ትዝ አሉኝ፤ አንድያ ተቋማቸውን ‹‹አሕባሽ››ለሚባል መጤ አስተምህሮ አራማጆች አሳልፈው የሚሰጡ፣ የ‹አሕባሽ›ን አስተምህሮ በግድ እንጫንባችሁ ሲሏቸውም ‹በጄ›የሚሉ አይመስለኝም በእርግጥም ካላበዱ በስተቀር! እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አላበዱም፡፡

Share

Breaking News:The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Exile Endorsed the Ethiopian Muslims’Movement

The holy Synood in Exile has endorsed the Ethiopian Muslims movement and called upon the faithful to join the movement. Negashi OJ believes that this is a huge step forward in creating a united front in the struggle for a democratic Ethiopia where all Ethiopians regard of their belief,etnicity or the like enjoy equal freedom.

Here is the clip with a note from ECADForum..com:

Washington D.C. –The Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Exile has concluded its 33rd regular conference successfully. It has discussed several national issues in the three days meeting. At the end of the conference,the Holy Synod made a press release in which it condemned the killing of Muslim brothers and sisters in Ethiopia and called upon all Orthodox believers to join the fellow Muslims in their protest against the unlawful intervention of the TPLF/EPRDF regime in their religious norms.

http://www.youtube.com/watch?v=Qd_U7NHZSng

Share

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ! –በብራስልስ አውሮፓ ካውንስል ፊት ለፊት –May 16,2012

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ!

 

በአውሮፓ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት፣ የኢትዮጵያዊያን ኮሚውኒቲ በቤልጂየም እና የሉቅማን የኢትዮጵያዊያን-ቤልጂማዊያን ሙስሊሞች ማህበር በጥምረት ጥሪያችንን እናቀርባለን፤

ሰልፉ የሚካሄድበት ቀንና ሰአት፦ ሜይ 162012 1300 ሰዓት ጀምሮ

ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ፦ በብራስልስ አውሮፓ ካውንስል ፊት ለፊት

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል። በግለሰቦች ላይ ከሚደርሰው የመሰወር፣ የጅምላ እስራት፣ በድብደባ ማሰቃየት፣ አፈና እና ግድያ፣ ከስራ መባረር፣ ንብረት መነጠቅ እና ሌሎች በደሎችበተጨማሪ የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን፣ የኃይማኖት ተቋማትን፣ የሙያና የሲቪክ ማኅበራትን፣ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችን እና የፖለቲካ ፓሪቲዎችን ዒላማ ያደረገ የጥቃት እርምጃ በተደጋጋሚ በመንግስት በኩል እየተወሰደ ይገኛል። እነዚህ የመብት ጥሰቶች መፍትሄ ሳይበጅላቸው ለረዥም ዘመናት ከቆዩት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ቀውሶች ጋር ተዳምሮ አገሪቱን እጅግ አስፈሪ ወደሆነ ሁኔታ እያመራት ይገኛል። ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከመንግስት ቁጥጥር ስር ወጥተው አገሪቱ ማቆሚያ ወደ ሌለው ቀውስና እልቂት ውስጥ ከመግቧቷ በፊት የአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ተገቢውን ጫና በመንግስት ላይ ያደርግ ዘንድ ለማሳሰብ ይህን የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተናል። በዚህም መሰረት ለአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ የምናቀርባቸው ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

  1. መንግስት የተለያዩ ሰበቦችን በመፍጠር በአገሪቱ የተለያዩ ማጎሪያ ቤቶች ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች ባፋጣኝ እንዲፈታ፤

  2. መንግስት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ሰበብ በሃሰት በአሸባሪነት ወንጅሎ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ባስቸኳይ እንዲፈታ፤

  3. በአፋር ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላ እና በኒሻንጉል ክልል ውስጥ ልማትን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን ዜጎችን ከመኖሪያ ቀያቸው የማፈናቀል እርምጃ ባፋጣኝ እንዲቆም፤ የመንግስትን ሕገ ወጥ እርምጃ በመቃወማቸው የተነሳ ለእስር የተዳረጉ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ባፋጣኝ እንዲፈቱ፤

  4. መንግስት በኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ በመግባት እያደረገ ያለውን ሕገ ወጥ ተግባር ባፋጣኝ እንዲያቆም፤ በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ፣ ጫና እና ጣልቃ ገብነት ግዲያና ዛቻ እንዲቆም፤ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ገዳማትና ታሪካዊ ስፍራዎች ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት እንዲገታ፤

  5. ሕጋዊ በሆነ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ብቻ ከሥራ ገበታቸው የተባረሩ መምህራ ባፋጣኝ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ፤ እንዲሁም መንግስት የመምህራኑን አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ከማፈን ተቆጥቦ ተገቢዎን ምላሽ እንዲሰጥ፤

  6. በኢትዮጵያ በነጻነት የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ፣ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ የመቃወም እና ሌሎች መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚደረገው ከፍተኛ አፈና እና ጫና እንዲቆም እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +32 477 327 090+32 486 454 955+32 486 336 367 ሊደውሉ ይችላሉ::

የኃይማኖት፣ የዘር፣ የቋንቋ እና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶቻችን የኢትዮጵያዊነታችን ውበት እና የአንድነታችን መገለጫዎች ናቸው!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
አስተባባር ኮሚቴው!!

Share

Nejashi Justice Council Strongly Condemns the April 27th Asasa Massacre by the Security Forces of Ethiopian Regime

WASHINGTON,May 7,2012 /PRNewswire/ —Nejashi Justice Council is extremely outraged by the April 27th slaughter of innocent Ethiopian Muslims in Asasa,Arsi zone,Oromia region. According to Badr Broadcast Network 11 innocent Muslims were killed and several injured when the armed force of the Ethiopian Regime arbitrarily opened fire on Muslims returning from Friday prayers. A six-year-old-boy,a woman and an old man were among the innocent civilians killed due to this savage attack of the Ethiopian Regime's force. And the credible report from the ground confirmed that scores of Muslims were arrested. Such a brutal assault on innocent civilians shows the Ethiopian authorities'contempt for the lives of their innocent citizens,says Nejashi Justice Council.

Nejashi Justice Council strongly condemns these acts of deliberate and provoked killings and injuries through the use of armed forces,and arbitrary incarceration of innocent civilians,which is undoubtedly a gross human rights violation. Nejashi Justice Council sends condolences to the families and relatives of all those killed on April 27,2012.

Continue reading Nejashi Justice Council Strongly Condemns the April 27th Asasa Massacre by the Security Forces of Ethiopian Regime

Share

Ethiopian Muslims Defiant and Determined Despite Mounting Threats from the Criminal Ethiopian Government

Ethiopian Muslims have once again turned in mass for a weekly demonstration againtst the ongoing Ethiopian government interference in their belief system and its defiance to the more than 4 month old movement for the respect for their constitutional rights. The May 04,2012 demonstration is particularly of interest in that a night earlier the government issued its nonsense statement ever and make it clear to every Muslim that it has no room to entertain the Muslims demands. Worse is that the government characterized its killing of innocent Worshippers a week earlier (April 27,2012) as action againt terrorism. This has definately worked against the wish of the government. It galvanised the mass and brought them out to demonstrate its definance to the government's atrocity and as a show of determination to pursue its demands despite the threat as well as real danger of being targated by the cruel regime.

http://www.youtube.com/watch?v=vfu_B1idMZ4
http://www.youtube.com/watch?v=ZbErvPj6o2k

[Ecadforum.com] Our Muslim brothers and sisters in Ethiopia are standing their ground in defiance against Meles Zenawi’s assault on their faith. There was a massive demonstration at Anwar Mosque in Addis Abeba Friday with a thunderous and earth-shaking roar. It is hard to imagine how so many people can become this united and voice their outrage with such vigor and determination. It is awesome. It reminds us of the previous uprising in 2005. And it sounds like the coming of a real revolution that is about to engulf Ethiopia like wild fire.

In the face of such fiery defiance,the main question now is how Meles Zenawi is going to respond. And what is more important is how our Muslim brothers and sisters are going to react after the monster kills a few of the courageous Muslims among the demonstrators. We will find out in the coming days and weeks. I would not be surprised if Meles Zenawi bribes a few people from the leadership of Ethiopian Muslims and create division. And then attack or arrest the rest of the leadership. And of course,as usual,Meles Zenawi will kill some Muslim brothers and sisters from the rank and file to intimidate most of the demonstrators if he can.

Listen that earth-shaking roar at Anwar Mosque directed at Monster Zenawi. The million dollar question is,“Will our Christian brothers,our students,workers,and our genuine Ethiopians in the army do the same?”It remains to be seen. If they do,God help them.

As if thousands of lies would make one truth,the government continued with its futile propaganda againt the peaceful movement. The latest asserts that two foreigh nationals were cought at Anwar Mosque on May 04,2012 while mobiling the people and distributing papers. The report claims that the two arrived at Bole International airport on the same day,headed directly to Anwar and went into action. The following a brief commentary (from Facebook) on this latest futile effort of the part of the government:

በዛሬው እለት ETV ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎች በአንዋር መስጅድ ህገ ወጥ ቅስቀሳ ሲያደርጉና ወረቀት ሲበትኑ መያዛቸውን ዘግቧል። አንዲሁም ሁለቱ የውጭ ዜጎች በ24 ሰአት ከሀገር እንዲዎጡም እንደተወሰነ ጨምሮ ታናግሯል። የውጭ ዜጎቹ ከመካከለኛው ምስራቅ መሆናቸው እንጂ የየት ሀገር ዜጋ አንደሆኑ በግልፅ አልተነገረም። እንደ ETV ዘገባ የውጭ ዜጎቹ ዛሬ ጠዋት (አርብ እለት ማለት ነው) አዲስ አበባ እንደገቡና በቀጥታም ወደ አንዋር መስጊድ እንደሄዱ ተገልፅዋል። ETV የሁለቱን ግለሰቦች ፎቶ አሳይቷል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተመስርቶ የሚከተሉትን አራት ጥያቄዎች ማንሳት እዎዳለሁ:-

1 የተባለው እውነት ከሆነ መንግስት ለምንድነው ግለሰቦቹን ለፍርድ ያላቀረባቸው?????
ይህንንም የምልበት ምክንያት የውጭ ዜጋ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ መግባት ህገዎጥ ስለሆነ ነው። ስለዚህ መንግስት እነዚህን ግለሰቦች ለፍርድ ቢያቀርብ የሀገሪቱም ሕግ ይደግፈዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ለማድረግ እንደማይፈራም በእስር ላይ ያሉትን ሁለቱን የስዊድን ዜጎች ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

2 የውጭ ዜጎቹ የየት ሀገር ዜጋ መሆናቸው ለምን አልተገለፀም?????
መንግስት የስዊድንን ዜጎች በግልፅ ለፍርድ ካቀረባቸው፣ ለምንድን ነው የአንዲት የመካከለኛ ምስራቅ ሀገር ዜጎችን ዜግነት በግልፅ መናገር ያዳገተው? ነገሩ እውነት ቢሆን ኖሮ የግለሰቦቹን ዜግነት መግለፅ ባላዳገተው ነበር። ነገር ግን ዘገባው የፈጠራ ስለሆነ በአንድ ሀገር ላይ ማላከክ፣ ከተዎንጃዩ ሀገር ትልቅ ጥያቄ ልያነሳና መንግስትን የዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ውስጥ ሊከተው ይችላል።

3 መንግስት እራሱ ሰዎቹን ላለማምጣቱስ ምን ማስረጃ አለን???
ይህንን ደግሞ ማድረግ ለመንግስት በጣም ቀላል ነው። አህባሾች እራሳቸው የመጡት ከሊባኖስ በመሆናቸው ሁለት የአረብ ወጣቶችን በቀላሉ ከሊባኖስ ሊያስመጡና መንግስት ለፕሮፓጋንዳነት እንዲጠቀምበት መንገዱን ሊያመቻቹ ይችላሉ። በዚያውም ለሁለቱ ወጣቶች ሽር ሽር ይሆናቸዋል። Of course,ትንሽ የገንዘብ ጉርሻም ይሰጣቸዋል።

4 ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ ሁለቱ የውጭ ዜጎች በ24 ሰአት ከሀገር እንዲወጡ መደረጋቸው ነው። ልብ በሉ፣ እንደ መንግስት ዘገባ እነዚህ ሰዎች ከውጭ ሀገር ድረስ ረብሻ ለመቀስቀስ የመጡ ናቸው። ታዲያ እንዴት ተደርጎ ነው በ24 ሰአት ከሀገር እንዲወጡ የሚደረገው? መንግስት እንደመንግስትነቱ እነዚህ ሰዎች ላይ ምርመራ ማድረግ የለበትምን? ለምሳሌ ማን ከህዋላቸው እንዳለ? ምን አይነት network እንዳላቸው? የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊቀርቡላቸውና ሊመረመሩ አይገባቸውምን? ሁላችንም እንደምናውቀው ሁለቱ የስዊድን ዜጎችና አንድ የUN ሰራተኛ በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ ናቸው። ታዲያ የስዊድን ዜጎችንና የUN ሰራተኛን መመርመርና ማሰር ያልፈራ መንግስት ለምንድን ነው እነዚህን የውጭ ዜጎች ማሰርና መመርመር ያልፈለገው??????

ይህ ሁሉ የሚያሳያን ዘገባው የፈጠራ ወሬ መሆኑን፣ የሙስሊሞች ተቃውሞ ላይ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠርና፣ እንዲሁም ክርስቲያን ዎገኖቻችን ላይ ጥርጣሬ በመፍጠር ከሙስሊሞች ጎን እንዳይቆሙ እየተደረገ ያለ ፕሮፓጋንዳ ነው። ለማንኛውም እኛም ነቅተንባቸዋል።

In the mean time the world leading media agency,Al Jazeera,has continued broadcasting the Ethiopian Muslims Movement for a straight four weeks.

Share