Earlier we published the press release of the Harar Majlis conference. The text we published was re-writen from the audio we had at the time. We have now received a copy of the text officially released. In stead of 12 points as we published,the press release has 15 points,bringing new elements and giving the whole issue additional dimension. Below is the full text.
የአቋም መግለጫ
ኢትዮጵይውይን ሙስሊሞችን በሚወክለው ብቸኛው ተቋማችን የኢትዮጵያ እስልምንቅ ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አስተባባሪነት ለሁሉም ክልሎችና ዞኖች እስልምና ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከሐምሌ 7 –19/2003 ዓ.ም በተደረገው ስልጠና፤
- ሀይማኖት ከህገ መንግስት አኳያ የተቀመጡትን ሕገ መንግስታዊ መብቶች በተመለከተ
ሀ/ የሀይማኖት ነፃነት
ለ/ የኃይማኖት እኩልነት
ሐ/ የኃይማኖት እና የመንግስት መለያየት በሚል በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
- እንዲሁም በሙስሊሞች መሀከል በመግባት ሙስሊሙን በመለያየት እና በመከፋፈል የራሳቸውን ዓላማ በማራመድ ችግር የሚፈጥረውን “የወሃብይ ቡድንን”አመሰራረት እና አላማውን በተመለከተ ከውጭ ሀገር በመጡ የሙስሊም እምነት ሙሁራኖች ሰፋ ያለ ትምሀርት በመውሰድ ወሃቢይና ፅንፈኞችን ለይቶ በመሰረታዊ የሃይማኖት (ዲን) እውቀት ማጥራትና መመለስ በሚችልበት ሁኔታ ትምህርቱን ስንወስድ ቆይተን የሚከተሉትን ባለ 15 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስልጠናውን አጠናቋል።
1ኛ/ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባረቀቀችው ህገ መንግስት የብሔር ብሔረሰቦችና የሐይማኖቶች እኩልነት መደንገጉ ይታወቃል። በመሆኑም ይህንኑ ህገ መንግስቱ የሰጠንን መብት በመጠቀም የዲሞክራሲ እና የልማቱን ስራ በማፋጠን ሀገራችንን ወደ ተሻለ ሰላምን የተመቻቸ ሀገር ማድረግ እንዲቻለን በመጀመሪያ የጠራ ሃይማኖታዊ እውቀት በመያዝ መሆኑ እሙን ነው። በመሆኑም ባሳለፍነናቸው የስልጠና ቀናት የሁሉም እምነቶች ነፃነት የሚረጋገጠው የሁሉም ሀያማኖቶች እኩል መብት ሲኖራቸውና የራሳቸውን ሃይማኖት ግን ለራሳቸው በመያዝ ከፈጣሪው ጋር እምነታቸው በሚያዘው መንገድ ግንኙነት ሲፈጥሩ እና በሌሎች እምነቶች ላይ ጫና ሳይጥሉ እንዲሁም መንግስት በሀይማኖት ሀይማኖትችም በመንግስት ጣልቃ በማይገባበት መንገድ ሲከተሉ ብቻ መሆኑን የሚገልጽ ሰፊ ህገ መንግስታዊ ትርጓሜ ያላቸውን ትምህርቶች ወስዶአል። በመሆኑም ይህንኑ በስልጠናችን ወቅት ያዳበርነውን የሕገ መንግስታችን ትንታኔ እስከ ታችኛው የሙስሊሙ ህብረተሰብ ለማድረስ ቃል እንገባለን፡፡
2ኛ/ እኛ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሐረር ካምፓስ በሐረር ከተማ ለሁለት ሳምንት ያህል ሲሰጥ የነበረውን መሰረታዊ የአህሉ ሱና አልጀማዓ (አሕባሽ) የዲን እውቀት የሚያስጨብጠው ታሪካዊ ስልጠና የሀገራችን ሙስሊሞች ከጥንት አያት ከቅድመ አያቶቻችን ተጠብቆ በጥንቃቄ ሳይበረዝና ሳይከለስ የተረከብነውን እምነታችንን አሁን ያለውም ትውልድ ይህንኑ ቀጥተኛ መስመር ተከትሎ እንዲጓዝ እና ወሃቢያ እና ወሃቢያ የወለዳቸው ፀረ-ሙስሊም ኃይሎች ሰበካና የተጣመመ ፍልስፍና ሰለባ እንዳይሆን ከሃይማኖታችን ምሁራን ያገኘነውን ጥልቅ እውቀት ለወከለን ሙስሊም ህ/ተሰብ ለማድረስ በዚሁ በአህሉ ሱና ወል ጀማዓ መንገድ ቃል እንገባለን፡፡
3ኛ/ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከፅንፈኞች እና አክራሪዎች ጎን በመሰለፍ ለሚፈጽሙት ህገወጥ ተግባር ሽፋን በመስጠት እና ደጀን በመሆን ሲተባበሯቸው የነበሩት ወገኖቻችን ከድርጊታቸው ታቀበው የሙስሊሙን ህ/ተሰብና ሀገርን በማመስ ሀይማኖቱን ሽፋን በማድረግ ከተደራጀ ቡድን ራሳቸውን አግልለው ወደ ቀድሞው ሰላማዊውና ቀጥተኛው መንገድ እንዲመለሱ በጋራ ጥሪያችንን እናስተላለፋለን፡፡
4ኛ/ አክራሪነትና ሽብርተኝነት በሀገራችን እንዲሰፍን ራሳቸውን ከመጋረጃ ጀርባ ደብቀውና ጭምብል ለብሰው እኩይ አላማቸውን ለማስፈፀም በተላላኪዎቻቸው በገንዘብና በማቴሪያል እርዳታ በመስጠት የሚያደራጇቸው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሰላም ወዳዱና ተቻችሎ አብሮ በመኖር አንጋፋ ተሞክሮ ያለውን ህዝባችንን በነውጥ ማዕበል ለማስመታት ሌት ተቀን የሚፍጨረጨሩ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መርዛማ እጃቸውን እንዲሰበስቡልን አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
5ኛ/ አክራሪነትና ጽንፈኝነት እነሱ ከሚከተሉት ውጭ ያለውን እምነት ተከታዮች መንግሥታዊ መብት የአገር ጸጥታና ደህንነት በአጠቃላይ በማደግ ላይ ያለውን ኢኮኖሚያችንን ክፉኛ የሚያንኮታኩት በመሆኑ በእንጭጩ ልናደርቀው ስለሚገባ በሁሉም ክልል ያሉ የጸጥታና የፖሊስ ኃይላት ከጠቅላይ ም/ቤታችን ጎን በመሰለፍ ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
6ኛ/ አክራሪነትን ኪራይ ሰብሳቢነት ጸረ-ዲሞክራሲያዊ አመላካከት እና አሰራርን በቅድሚያ ከመዋቅራችን ለማጥፋት እና ተቋማችንን በሁሉም መልክ ለማጠናከር መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል መዘጋጀታችንን በአንድነት እናረጋግጣለን፡፡
7ኛ/ ተቻችሎና ተከባብሮ በመኖር ወደር የማይገኝለት የሀገራችን ህዝቦች እንደቀድሞው ዛሬም እምነታችን የግላችን ሀገራችንን በጋራ ለማልማትና በየቤተዕምነቱ የመሸጉ የከሰሩ ፓለቲከኞችና አክራሪዎች እርቃናቸውን እንዲቀሩ ለማድረግ በሀገራችን ካሉ ከሁሉም የእምነት ተከታዮች በተውጣጡ የሰላምና የምክክር ጉባዔ በግምባር ቀደም ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
8ኛ/ እኛ የስልጠና ተሳታፊዎች ጠቅላይ ም/ቤቶችን አሁን ከተሰጠን ስልጠና ቀጥሎ በአስቸኳይ የጽንፈኞችና የወሃቢያዎች ርዝራዦች ከላይ እስከ ታች ያሉ መዋቅሮችን ህግና ሥርዓት በተከተለ መልክ እንዲያጸዳ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም ይህ ስልጠና ቀጣይነት እንዲኖረው እስከ ታችኛው ምዕመናን ድረስ ለማውረድ የበኩላችን ለመወጣት ሁላችንም ቃል እንገባለን፡፡
9ኛ/ በሀገራችን በሚገኙ የመድረሳ ት/ቤቶች የሚሰጡ ትምህርቶች በሁሉም አካባቢ የተለያዩ ካሪኩለም ይዘት ያላቸው እና የውጭ ሀገር የት/ት ካሪኩለም መሆኑ ይታወቃል፤ በመሆኑም ይህ የትምህርት አሰጣጥ ለሀገራችን የመድረሳ ት/ቤቶች አንድ ወጥ አቋም እንዲይዙ በማድረግ አዲስና ጠማማ አመለካከት በመፍጠር ተተኪው ትውልድ ላይ ጫና እየፈጠሩ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በሀገራችን የመድረሳ ት/ቤቶች የሚሰጠው የመድረሳ ትምህርቶች የሀገራችን ዑለማዎች በሀገራችን ሲሰጥ በነበረው የሃይማኖት ትምህርት መሰረት በማስጠናት አንድ ወጥ የሆነ ካሪኩለም በማስቀረጽ ለመድረሳ ትምህርቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው እንጠይቃለን፡፡
10ኛ/ በሀገራችን የሚደረጉ ዳዕዋዎች፣ የሚሰሩ መስጅዶችና መድረሳዎች በየመስጅዱ የሚያሰግዱ ኢማሞች እና የመድረሳ መምህሮችን ፍቃድ መስጠትን በተመለከተ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት ፈቃዱን የመስጠት ኃላፊነቱን በበላይነት እንዲመራና ከእስልምና ጉዳዮች ፈቃድ ውጭ ዳዕዋ እሚያደርጉ፣ መስጂድ መድረሳ የሚሰሩ፣ በኢማምነት እና በመድረሳ እሚያስተምሩ መምህራን ከአድራጎታቸው እንዲታረሙና እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን፡፡
11ኛ/ በሀገራችን ያለ መጅሊሱ እውቅና የሚደረጉ ህገወጥ ኮንፈረንሶችና እስካሁን ካለመጅሊስ እውቅና በተደረጉ ኮንፈረንሶች የተሰበሰው ገንዘብ በምን ላይ እንደዋለ በመንግሥት በኩል አስፈላጊውን ህጋዊው ጥያቄና ክትትል እንዲደረግ ከአሁን በኋላ ግን ማንኛውም ኢስላማዊ ኮንፈረንሶችና ገንዘብ ማሰባሰብ ያለ መጅሊስ እውቅና እንዳይደረጉ እንጠይቃለን፡፡
12ኛ/ አንዳንድ መንግስታዊ ያልሆኑ N.G.O ከሀይማኖቱ ጋር በተያያዘ መንግስት እንዲሰሩ ከሰጣቸው የሥራ ፈቃድ ውጪ በእስልምና ጉዳዮች ሥር ጣልቃ በመግባት እያደረጉት ያለው ሙስሊሙን ከሙስሊሙ የማጋጨት ሥራ እጥብቀን እያወገዝን ወደፊትም እነዚህ በ N.G.O ስም ፈቃድ ወስደው የማይመለከታቸውን ሥራ በመስራት ሙስሊሙን ከሙስሊሙ ለማጋጨት እሚያደርጉትን ችግር የመፍጠር ተልዕኮ ጉዳዮ የሚመለከተው የፍቃድ ሰጪ አካል ፍቃዳቸውን በመሰረዝ ላጠፉት ጥፋት በህግ እንዲጠየቁልን እንጠይቃለን።
13ኛ/ በልማታዊ መንግሥታችን የተነደፈውን የ5 ዓመት የእድገትና የትራንስፎንሜሽን እቅድ ተግባራዊነት ለልማት ቆርጦ ከተነሳው ህዝባችን ጋር በመሆን ለስኬቱ ተግተን ለመስራት ቃል እንገባለን፡፡
14ኛ/ ከህዝባችን አልፎ ለጎረቤት አገራት ተስፋ አለኝታ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የህዳሴ ግድባችን ወደ አንድ ታላቅ የዕድገት ደረጃ የሚያሸጋግረን በመሆኑ የወከለንን ህዝብ በሙሉ በማስተባበር እና በዉጭ ሐገር የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያኖትን ለዚህ ወሳኝ ፕሮጀክት የበኩላቸውን አስተዋፅ ኦ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ሁሉ ለመፈፀም ቃል እንገባለን።
15ኛ/ ሁሉም ዕምነቶች በእኩልነት በሚከበርበት ሥርዓት ላይ ያለን በመሆኑ ሙስሊሙ ህ/ስብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ሐገሩን የመጠበቅና የመከላከል ብሎም አገርን በማልማት እራስንና ወገንን በመጥቀም ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማድረግ የሚጠበቅብን ወቅት በመሆኑ የሀገራችን ባለሀብቶች እና የሙስሊም ሀገራት ባለሀብቶች ለልማት ምቹ በሆነችው አገራችን ሳይሸማቀቁ እንቭስት እንዲያደርጉ ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም ለመቀስቀስ እና ለማሳመን ቃል እንገባለን።
ሐረር
ሐምሌ 2003



















Is the above press release written by Ato Meles Zenawi or any one who is unfamiliar to Islam. It looked like it iwas written by the EPRDF poliburo.Nowhere in the press release we see the Words of Raull(SAW)or a verse from Koran.These guys they can climb any mountain,but they will not divide the muslim Ummah.I think it is about time to Expose who the ahbash al Hararis are.Is it a congregation of one ethnic group from Ethiopia? Please someon enlighten us on this matter. I heard also their KIbla is south east contrary to the Muslim belief.