ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ያነሷቸው ጥያቄዎች የመብት ጥያቄዎች ናቸው። “በሃይማኖታችን አትግቡብን ማለት”መብት ነው። “የማንፈልጋቸው የማኅበራችንን መሪዎች ሽረን የምንፈልጋቸውን እንምረጥ”ማለት መብት ነው። “በትምህርት ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ”ማለት መብት ነው።
ሙስሊም ኢትዮጵያዊን ከላይ የተጠቀሱትን የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ሰበብ እየተፈለገ እየታገቱ፤ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው፤ ከዚያም አልፎ እየታሰሩ ነው። ዜጎች የራሳቸውን እምነት ራሳቸው መምረጥ በመፈለጋቸው “አሸባሪ፣ አክራሪ፣ ቅጥረኛ”ሌላም ሌላም እየተባሉ ለሰቆቃ እየተዳረጉ ነው። በመረጥናቸው መሪዎች ብቻ እንመራ ማለትም በግንቦት 7 አባልነት የሚያስፈርጅና የሚያስከስስ ወንጀል ሆኗል።
በግንቦት 7:የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እምነት፣ የሙስሊም ዜጎቻችን ጥያቄዎች የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጥያቄዎች ናቸው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ምርጫው የሆነ እምነትን የመከተልና የማምለክ መብት አለው። የማምለክ መብት የሰብዓዊ መብቶች አካል ነው። ሰብዓዊ መብቶች ደግሞ መሸራረፍ የለባቸውም።
የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን በራሱ ካድሬዎች ለመሙላት እያደረገ ያለው ጥረት በቤተክርስትያኗኗ በምእመኖቿ ላይ ያደረሰውና እያደረስ ያለው ችግር ቀላል አይደለም። ከፍተኛ የሃይማኖት መሪዎች በወያኔ የስለላ ዱርዬዎች የደረሰባቸውን የአካል ድብደባው የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው። ዛሬ ደግሞ ይህ ዘረኛ አገዛዝ ፊቱን ወደ እስላም ሃይኖትና ሙስሊም ኅብረተሰብ አዙሯል።
የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ሃይማኖት ሲመርጥልን ዝም ብለን ልንቀበል አይገባም። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በእስልምና ሃይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መቃወማቸው ተገቢ ነው። እንዲያውም ይህ ጥያቄ የሙስሊም ኢትዮጵዊያን ብቻ ሳይሆን የሌሎች ሃይማኖቶች ተከታዮች የሆኑ ኢትዮጵያዊያንም ጥያቄ ነው።
የሙስሊም መብት ተደፍሮ የክርስቲያኑ፤ የክርስቲያኑ መብት ተደፍሮ የሙስሊሙ ሊከበር አይችልም፤ አይገባምም። መብቶች ሃይማኖት የላቸውም። ስለሆነም ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጎን መቆም ለነፃነትና ዲሞክራሲ ግድ ያላቸው ዜጎች ሁሉ ኃላፊነት ነው።
የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እጁን እንዲያነሳ ከመጠየቅ በተጨማሪ:
1ኛ. በወያኔ የተጠለፈው የኢትዮጵያ እስላማዊ ምክር ቤት (መጅሊስ) እንዲፈርስና አዲስ ምርጫ እንዲደረግ፤ እና
2ኛ. አወሊያ የትምህርት ተቋም ከወያኔ ተጽዕኖ ነፃ እንዲሰራ
ያቀረባቸው ጥያቄ ተገቢና መሠረታዊ ናቸው ብለን እናምናለን። እነዚህ ጥያቄዎች የሁሉም ሃይማኖቶች ተከታዮች ጥያቄዎች ናቸው።
የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ አገራችንን አንድም ነፃ ተቋም የሌላት አድርጓቷል። በአሁኑ ሰዓት ወያኔ የማይቆጣጠረው አንድም የሃይማኖት፣ ህዝባዊ፣ የልማትም ሆነ ማኅበራዊ ተቋም የለም። ነፃ ተቋማት በሌሉበት ነፃ አገር የለም። ስለሆነም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለተቋሞቻቸው ነፃነት የሚያደርጉት ተጋድሎ የሁላችንም ተጋድሎ ነው። በዚህም ምክንያት የሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን ትግል መደገፍ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም የትግሉ አካል መሆን ይኖርብናል ብለን እናምናለን።
በጉልበተኛ ወንበዴዎች በሚገዛ አገር ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት ይኖራል ማለት ዘበት ነው። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ሳይወገድ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄ ምላሽ ያገኛል ብለን አናምንም።
ስለሆነም የትግሉ ስትራቴጂያዊ ግብ የመለስን አምባገነን ሥርዓት በማስወገድ በምትኩ ለሃይማኖቶች እኩልነት የቆመ መንግሥት መመሥረት ነው ብለን እናምናለን። ይህ ደግሞ የግንቦት 7 ንቅናቄ ዓላማ ነው። የግንቦት 7 ሙስሊም አባላት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በጀመሩት ትግል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የሌሎችም ሃይማኖት ተከታዮች የሙስሊሙን ጥያቄ በሚመቻቸው መንገዶች ሁሉ መደገፍ ይኖርባቸዋል። በዚህ አጋጣሚ ደግሞ ለእኩልነት፣ ለነፃነትና ዲሞክራሲ ግድ ያላችሁ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላትም ግንቦት 7ን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን።
የኢትዮጵያ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የጀመረው ትግል የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ አይደለም። ትግሉ የነፃነት፣ የሰብዓዊ መብት እና የእኩልነት ጉዳይ ነው። እናም ሁላችንንን ያገባናል፤ በጋራ ቆመን ትግሉን እናፋፍም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!





















ቢስሚልላህ,አልሃምዱሊላህ,
ወሰለላቱ ወሰላም አላ ረሱሊላህ,
ጀዛኩም-አላሁ ኸይረን ወንድሜ "አበሮስ 99"እና ነጋሺ ራድዮ አዘጋቾች::
የሰለፊያ ጋዜጣ ሪፕርት በደምብ ከሰማነው:መንግስት (ኢሃደግ) አሻፈረኝ ብሎ የአህባሽን ጠመቃ ተግባር ላይ ለማዋል ጥረቱን መቀጠሉን ነው::"አበሮስ 99"ከሰለፊያ ጋዜጣ ጠቅሶ ካቀረባችው ዘገባ:ኢሃደግ በወለጋ እና በጅማ ካላቸው ጥቂት እንጥቀስ:
"መንግስት እንዲያስተምር ፈቃድ የተሰጠው አህባሽን መቃወም ህግ መጣስ ነው"
"ዎሃቢያ [ድምፃችን ይሰማ የሚሉ ሰላማዊ ሙስሊሞች] ከግንቦት 7 እና ክኦነግ አንድ ነው::[...] በእቅዱም በመጀመርያ ከኦሮሚያ ወድ ዞን"ከዞን ወደ ወረዳ:ከወረዳም ወደቀበሌ:ከቀበሌም ወደ ህዝብ ሲሆን:የመጅሊስ ምርጫም ይካሄዳል::ምርጫዉን ለማክሸፍ ይንቀሳቀሳሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ካሉ እንዲታሰሩ ተደርጎ የተወሰኑት ምርጫው ሲያልቅ ይፈታሉ የሚባልም ነገር አለ::ወሃቢያ ከኸዋሪጅ አንድነው:ስለዚህ መንግስት በጠላትነት እና በአክራሪነት ፈሪጆታል::"
[ጥቅስ ተፈጰመ]
ክዚህ በላይ ያለዉን ተመሳሳይ ደባ ተጠቅሞ:ከዚህ በፊት ኢሃደግ ምርጫ ሰርቆ በመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ላይ አልተሳለቀም ወይ? ከዚያም አልፎ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በአደባባይ አልጨፈጨምን?
የመርካቶ ኪስ አውላቂ የሰረቀዉን ሰው እየሰደበ መደብደብ አይነት ነው::
እንግዲህ በትዕግሥት ለረጅም ትግል መዘጋጀት ነው::ትዕግሥት ማድረግ ከባድ ቢሆንም በአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘንድ ትልቅ ምንዳ አለው::
ረዋሁ እብን አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁም)"
"ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙዓዝን ወደ የመን ሲልኩት እንዲህ አሉትም:'ፍራቻ ይኑርህ:ከተጨቆነ (ሰው) እርግማን:በሱ ዱዓ እና በአላህ መካከል መጋረጃም የለም::"ስሒህ ቡኻሪ
የመንግስት (ኢሃደግ) አሻፈረኝ ብሎ በግድ ሁሉንም ጠላት አድርጎ መፈረጅ የጣር ምልክት ይመስላል::
ኢብን አባ ቆጨም